ይህ መመሪያ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የመሬት፤ ዓሣ እና ደን አስተዳዳርና ጥበቃ፤ ለብሄራዊ የምግብ ዋስትና በሚል ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ነው፡፡
የነዚህ የበጎ ፈቃድ መመሪያዎች አላማ የመሬት፣ የአሳ እንዲሁም የደን ይዞታ አስተዳደርን ለማሻሻል ምሪት መስጠት ብሎም እንደማጣቀሻ ማገልገል ሲሆን ይህም ለሁሉም ሰው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የተሰኘው መርሆን መሠረት ያደረገ እና የሰው ልጆችን በቂ ምግብ የማግኘት መብት በአገር አቀፍ የምግብ ዋስትና ማዕቀፍ ውስጥ በዘላቂነት እውን እንዲሆን ድጋፍ መስጠት ነው። የነዚህ መመሪያዎች አላማ ረሃብን እና ድህነትን ለማጥፋት ለሚደረገው አለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ርብርብ አስተዋጽዖ ማድረግ ሲሆን ይኸውም ቀጣይነት ያለው የመሬት ልማት ለዕድገት መሠረታዊ ጉዳይ ነው የተሰኘውን መርሆ በማንገብ ፍትሃዊ የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብት ክፍፍል እንዲሁም ዋስትና ያለው የይዞታ መብት እንዲኖር ማስተዋወቅን ይጨምራል። ድህነትን እና ረሃብን ማጥፋት እንዲሁም ቀጣይነት ያለው የተፈጠሮ ሀብት አጠቃቀምን ማስፈን በዋናነት የማህበረሰቡን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን መሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብቶች ማግኘት ላይ የተመሠረተ ነው። የአብዛኛው በተለይ የገ